ለ15 ደቂቃዎች ለሚዲያ ክፍት የነበረው የዋልያዎቹ የሦስተኛ ቀን ልምምድን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ እናድርሳቹሁ።
በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ ግንቦት እና ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን ከማላዊ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦሰረተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ ከሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ እየሰራ ይገኛል።
– አሰልጣኝ ዮሐንስ ጥሪ ካደረጉላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል በዛሬው መርሐ ግብር 21 ተጫዋቾች ብቻ ተሳትፈዋል።
-ትናንት በግል ጉዳይ ከቡድኑ ጋር ልምምድ እንዳልሰራ የነገርናቹሁ ግብጠባቂው አቡበከር ናስር ጉዳዩን ጨርሶ በዛሬው ልምምድ ተሳትፎ አድርጓል።
– ለአስራ አምስት ደቂቃ ለሚዲያ ክፍት በሆነው የልምምድ ወቅት እንደተመለከትነው ከሆነ አሰልጣኝ ዮሐንስ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ተጫዋቹ የማሟሟቅ ስራ እና ፈጣን ቅብብሎሽ ያለበት መሀል ገብ ስራዎችን ሰርተው ለሚዲያ የተፈቀደው ደቂቃ አብቅቷል።

– ብሔራዊ ቡድኑ የአዲስ አበባ የሦስት ቀን ልምምዱን በንግድ ባንክ ሜዳና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሰርቶ ዛሬ አጠናቋል።
– ነገ ጨዋታውን ወደ ሚያደርግበት ድሬደዋ ከተማ የሚያቀና ሲሆን ከጨዋታው አስቀድሞ ባሉ ሁለት ቀናቶች በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ልምምዱን የሚሰራ ይሆናል።
– ጨዋታዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ እንደመሆኑ መጠን እስካሁን ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች እና ኮሚሽነሮች ከሀገር ውስጥ ይሁኑ ከውጭ ሀገር አልታወቁም።
– አሰልጣኝ ዮሐንስ ሰሀሌ በድሬደዋ ቡድኑ ከሚያደርገው ከመጨረሻ ልምምድ አስቀድሞ አልያም በኋላ ለመገናኛ ብዙሀን በጨዋታዎቹ ዙርያ ማብርራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
– ሶከር ኢትዮጵም እንደከዚህ ቀደሙ ወደ ስፍራው ሪፖርተሯን በመላክ እያዳንዱን የብሔራዊ ቡድኑን እንቅስቃሴ መረጃዎችን ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል።

