ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ስዊድን ተመለሰ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ስዊድን ተመለሰ

አማካዩ ሀሩን ኢብራሂም በውሰት ውል ዳግም ወደ አልስቬንስካን ተመለሰ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ ቆይታ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሀሩን ኢብራሂም በስድስት ወር የውሰት ውል ከሻርጃህ ወደ ‘BK Hacken’ አምርቷል። በአንድ ወቅት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ይህ የ23 ዓመት አማካይ በአል ባታህ እና ሻርጃህ ቆይታ ካደረገ በኋላ ዳግም ወደ ስዊድን አልስቬንስካን ተመልሷል።

በኢንግሊዝ League One ተሳታፊ ለሆነው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ከከሸፈ በኋላ ወደ ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ አቅንቶ ያለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ ቆይታ ያደረገው ይህ ወጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ካልተሳካው ቆይታ በኋላ ዳግም ራሱን ለማሳየት ወደ ስዊድን ተመልሷል። በኖርዌዩ ክለብ ቆይታው ከሞልደ ጋር በቻምፕዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ ተሳታፊ የነበረው ሀሩን ከዚህ ቀደም በሞልደ ፣ ‘GAIS’ ፣ ሻርጃህ እና አልባታህ ቆይታ ማድረግ ችሏል።