የብሔራዊ ቡድኑ ቁጥር አንድ ተመራጭ ግብጠባቂ ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ ሊጓዝ እንደሆነ ሶከር ኢትዮጵያ መረጃ አግኝታለች።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብ ጠባቂነት እያገለገለ የሚገኘው እና በሦስት ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ የሊጉ ኮከብ ግብጠባቂነትን ክብር ያገኘው አቡበከር ኑራ በዛሬው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ እጅግ ምርጥ ብቃቱን በማሳየት በግሉ ቡድኑን ከሽንፈት መታደጉ ይታወቃል።
አቡበከር ከብሔራዊ ቡድኑ የሦስት ቀናት የልምምድ ጊዜ በአንደኛው ቀን በግል ጉዳይ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሳይሰራ መቅረቱን ዘገባ አቅርበን እንደነበር ይታወሳል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባደረገችው ማጣት የግብ ዘቡ በደቡብ አፍሪካው ክለብ የዝውውር ጥያቄ ቀርቦለት ይንን ዝውውር ለማጠናቀቅ ደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ ገብቶ እንደሆነ ያወቅን ሲሆን ተጫዋቹም ምርጥ ብቃቱን ካሳየበት የዛሬው ጨዋታ በኋላ ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ አቅርበንለት የሙከራ የድህረ ገፃችን መረጃ ትክክል እንደሆነና የሙከራ እድል እንዳገኘ ገልፆልናል።

ከብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ እንዲሁም ነሊጉ ሁለት ጨዋታዎች ለኢትዮጵያ መድን ግልጋሎት ከሰጠ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያቀና አውቀናል። አቡበከር የሚሄድበት ክለብ ማን እንደሆነ ለጊዜው መረጃውን ያላገኘን ሲሆን በቀጣይ ተከታትለን ወደ እናተ የምናደርስ ይሆናል።
አቡበከር ከዚህ ቀደም ለወሎ ኮምቦልቻ፣ ለጅማ ከተማ ፣ ለባህር ዳር ከተማ በመጫወት ሲያሳልፍ ያለፉትን ሁለት ዓመታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ስኬታማ አመታቶችን እያሳለፈ ይገኛል።

