👉 “ከማላዊ ስንነሳ ቅዝቃዜ ነበር አሁን እዚህ ስንመጣ ደግሞ የአየሩ ሁኔታ በጣም ሞቃት ነው።”
👉 “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ቡድን ነው እናከብራቸዋለን።”
👉 “ይህ ጨዋታ ተጫዋቾቹ በስነ-ልቦና በታክቲክ እና በአካል ብቃት ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማየት ያስፈልገናል።”
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ የማላዊ ዋና አሰልጣኝ ካሊስቶ ፓሱዋ የሰጡትን አስተያየታት እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል።
የመጣነው ከ23 ተጫዋቾች ጋር ነው እዚህ ካየናቸው ነገሮች አንዱ የአየሩ ሁኔታ ሞቃት መሆኑ ነው:: ከማላዊ ስንነሳ ቅዝቃዜ ነበር አሁን እዚህ ስንመጣ ደግሞ የአየሩ ሁኔታ በጣም ሞቃት ነው። ስለዚህ ተጫዋቾቹ በፍጥነት ራሳቸውን ከአየሩ ሁኔታ ጋር እንዲያላምዱና ወደ ጨዋታው መንፈስ እንዲገቡ በፍጥነት ማስተካከል ያለብን ሌላው ነገር ይህ ነው።
ልምምዳችንን ከጨረስን በኋላ ምናልባት ተጫዋቾቻችን ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ እናያለን። እንዲሁም ምናልባት ጤንነት ይሰማቸው ያልነበሩ አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾች ነበሩን እናም የቀኑ ማጠናቀቂያ ላይ በነገው ጨዋታ ላይ እንዴት እንደሚሆኑ ለማወቅ እንሞክራለን።

እኛ ነገ ከ ከኢትዮጵያ ጋር ነው የምንጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ቡድን ነው እናከብራቸዋለን። እኛ ለልጆቻችንም ተነጋግረናል እነዚህን አሁን የምንጫወታቸውን ጨዋታዎች ሲጋፈጡ አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ተነጋግረናል።
እንደምታውቁት ምናልባት በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ውድድር እየተዘጋጀን ነው። ስለዚህ እኛ እኛም ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል እንዲሁም ተጫዋቾቹ በስነ-ልቦና በታክቲክ እና በአካል ብቃት ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማየት ያስፈልገናል።

