“ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የተጫወቱ ልጆች አሉ ፤ ፌዴሬሽኑ ረጅም ጊዜ ከሰጠን ..”

“ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የተጫወቱ ልጆች አሉ ፤ ፌዴሬሽኑ ረጅም ጊዜ ከሰጠን ..”

👉” ቁጥሩን ያላበዛንበት ዕድል ለመስጠት ነው..”

👉’ ሳንጠራቸው የቀሩ ካሉ የቀረ አራት ጨዋታ አለ እዛ ላይ…

👉 “እኛ ሙከራ አይደለም የያዝነው ብሔራዊ ቡድን ላይ ሊቆይ የሚችል ፍለጋ ላይ ነን…”

የዋልያዎቹ አለቃ ጉዳት አስተናግደው ከስብስብ ውጭ በሆኑ ተጫዋቾች ምትክ ለምን ሌሎች ተጫዋቾች አልጠሩም በሚለው ዙርያ ምላሽ ሰጥተዋል።

በድሬዳዋ ዓለማ አቀፍ ስታዲየም ነገ ከማላዊ አቻው ጋር የመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታ ዙርያ ዋና አሰልጣኙ ለመገናኛ ብዙሀን ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከስብስብ ውጭ በሆኑት አዲስ ግደይ እና መስፍን ታፈሰ ምትክ ለምን ሌሎች ተጫዋቾች ለምን አልጠሩም በሚለው ዙርያ ምላሽ ሰጥተዋል።

” አሁን ያሉት ሰማንያ ፐርሰንት ናቸው ፤ ወደ ብሔራዊ ቡድን የሚመጡት ሁሉም ሰርቶ ጥርት ብሎ ማየት እንድንችል ነው። ሰላሳ እና አርባ ሰው ከጠራህ በግልፅ እያንዳንዱን ማየት አትችልም። ልምምድ ስንሰራ በትክክል እየሰራ የምንፈልገውን ተግባራዊ እያደረገ ያለው ማነው ? ማነው ሊቆይ የሚገባው ፤ ማነው ትንሽ ዕድል ብንሰጠው እያሻሻላል የሚለውን በተግባር ሜዳ ላይ ማየት ያስፈልጋል። ስለዚህ አራት ቀን በሙሉ ሜዳም ሆነ ጠዋት በምናስተምረው ከሰዓት በምንጠይቀው መንገድ በግልፅ እንድናገኛቸው አድርጎናል። አምጥተህ ሃያ ደቂቃ መሞከር አይደልም ፤ እኛ ሙከራ አይደለም የያዝነው ብሔራዊ ቡድን ላይ ሊቆይ የሚችል ፍለጋ ላይ ነን። አሁንም ሃያ አንድ ልጆች አሉን አራት ቀን በደንብ አይተናቸዋል። ጥሩ ዕድል አገኝተናል። ቁጥሩን ያላበዛንበት ዕድል ለመስጠት ነው”።

በተጨማሪ አሰልጣኙ “የእያንዳንዱን ተጫዋች ማንነት በደንብ ነው የምናቀው የአካል ብቃቱን፣ የተጫወተውነ ጨዋታ ፣ ጉዳቱን እናቃለን፣ ያገቡትን ጎል እናውቃለን። እያንዳንዱን ነገር በዳታ ነው የምንሰራው። የማናቃቸው ተጫዋቾች የለም። ነገር ግን ሳንጠራቸው የቀሩ ካሉ የቀረ አራት ጨዋታ አለ ችግር የለብንም እዛ ላይ እንመለከታቸዋለን። በአንዴ ቡድን መቀየር አይቻልም። ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የተጫወቱ ልጆች አሉ ፌዴሬሽኑ ረጅም ጊዜ ከሰጠን ለወደፊቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ ልጆች መጥተው እንዲሰሩ እናደርጋለን። የእኔ በዚህ መቆየት ለኔ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ ለሀገር የሚጠቅሙ ልጆችን ለማዘጋጀት እንሞክራልን።” ብለዋል።