👉” በማሸነፍ ውስጥ ብዙ የምንማረው ነገር አለ
👉 “የሀገራችን ሊግ የምናአካል፤ ደረጃ አይተናል አካል ብቃት የለንም..”
👉 “ጨዋታውን ያሸነፍነው በታክቲካል ዲሲፒሊን ነው..”
👉 “መስራት የሚገባንን ነገር እንዳለ በግልፅ አይተናል..”
ጋዜጣዊ መግለጫው ሳይጠናቀቅ ጥለው የወጡት አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ በቆይታቸው ካነሷቸው አንኳር ነጥቦች መካከል ጥቂቱን እነሆ!
አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ “እንደነዚህ ያሉ ጨዋታዎችን ባናገኝ ኖሮ የትን እንዳለን አናውቅም ነበር። የምናቀው የራሳችንን ሊግ ብቻ ነው። ለእኛ ይህ ጨዋታ በጣም ወሳኝ ነው። ከእኛ ዝቅ ያለ ሳይሆን ከፍ ያለ ቡድን ነው የገጠምነው። ማሸነፋችን በጣም ጥሩ ነው። ሆኖም በማሸነፍ ውስጥ ብዙ የምንማረው ነገር አለ” ካሉ በኋላ ጨዋታውን ያሸነፉት በታክቲካል ዲሲፒሊንን ከነ ስህተታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

አሠልጣኙ በማስከተል ከቡድናቸው በዛሬው ጨዋታ ምን እንደታማሩ ሲናገሩ “የሀገራችን ሊግ የምናይበት ደረጃ አካል ብቃት እንደሌለ በግል አይተናል ፤ አካል ብቃት የለንም ስንል ግን ልጆቻችን በተፈጥሮ አካል ብቃት የላቸውም ሳይሆን አልሰራንበትም ፤ እንዳል ሰራን ደግሞ በግልፅ ታይቷል። በማስከተል በቀጣይ በእንደዚህ የአካል ብቃት አይደለም በአፍሪካ ዋንጫ መጫወት ያለብን በአጠቃላይ መስራት የሚገባን ነገር እንዳለ በግልፅ አይናል” ብለዋል።
* አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ በመግለጫው የመጨረሻ ክፍል በትናንትናው ዕለት ሶከር ኢትዮጵያ እና ባልደረባችን ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን ተንተርሶ የሰጡትን የግል ሀሳብ በተመለከተ ተከታይ ጥያቄ (Followup question) አቅርበንላቸው የነበረ ቢሆንም መግለጫውን ሳይጨርሱ ወተዋል።

