የዘጠኝ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ንግድ ባንክ የአራት ተጫዋቾቹን ውል አድሷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴካፋ ቻምፒዮንስ ሊግ ለሚጠብቀው ውድድር ይረዳው ዘንድ ቡድኑን ማደራጀቱን የጀመረ ሲሆን የአራት ተጫዋቾቹን ውል ማደሱንም ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የመስመር ተከላካዮቹ ናርዶስ ጌትነት እና ታሪኳ ዴቢሶ እንዲሁም የተከላካይ አማካይዋ ትዕግስት አዳነ በተመሳሳይ ለሁለት ዓመታት ፣ የመሃል ተከላካይዋ ሀሳቤ ሙሶ ደግሞ ለተጨማሪ አንድ ዓመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመቆየት ተስማምተው ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው።

