የወቅቱ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

የወቅቱ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

ከሁለት ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የሊጉ ኮከብ ተጫዋች በሲዳማ ቡና ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።

ሲዳማ ቡናዎች የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርገው እንዲያነሱ ትልቁን ሚና የተወጣው እና የዘንድሮ ዓመት የሊጉ ኮከብ ተጫዋችነት ክብር ያገኘው ያሬድ ባየህ ከሲዳማ ቡና ጋር  ያለው የውል ዘመን ሰኔ 30 መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ተጫዋቹን ለማስፈረም ሌሎች ክለቦች ፍላጎት ቢያሳዩም ተጫዋቹ ግን ዛሬ ከክለቡ አመራሮች ጋር ባደረገው ድርድር ለተጨማሪ ዓመት በሲዳማ ቡና ለመቆየት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።