ቻምፒዮኖቹ ወሳኝ ተከላካያቸውን ለማቆየት ተስማምተዋል

ቻምፒዮኖቹ ወሳኝ ተከላካያቸውን ለማቆየት ተስማምተዋል

በዘንድሮ ዓመት አብዛኛውን ጨዋታዎች ለሲዳማ ቡና በመጫወት ያገለገለው ተከላካይ በሻምፒዮኖቹ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።

ትናንት የመስመር አጥቂውን መስፍን ታፈሰን ውል በማራዘም ወደ ዝውውሩ የገቡት ሲዳማ ቡናዎች ከደቂቃዎች በፊት የወሳኝ ተከላካያቸውን ያሬድ ባየህን ለማቆየት መስማማታቸውን ዘግበን ነበር። አሁን ሌላኛውን የያሬድ ባየህ ተጣማሪ የሆነውን የቡድኑን ቁልፍ ተጫዋች ደስታ ደሙን በክለቡ ለማቆየት መስማማታቸውን አውቀናል።

በሙገር ሲሚንቶ ፣ በወልዋሎ እንዲሁም በቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ጭምር የቆየው ደስታ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሲዳማ ቡና ጋር ጥሩ የሚባሉ ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን አሁን ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።

ያሬድ ባየህ ከዚህ ቀደም በሴንትራል ፣ በአውስኮድ ፣ በዳሽን ቢራ ፣ በፋሲል ከነማ የተጫወተ ሲሆን ከዐፄዎቹ ጋር በቆየባቸው ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ሲታወቅ በመቀጠል በባህር ዳር እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመት ደግሞ በሲዳማ ቡና መቆየቱ ይታወሳል።