ነፃነት ገብረመድህን ውሉን ለማራዘም ተስማማ

ነፃነት ገብረመድህን ውሉን ለማራዘም ተስማማ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ጥሩ ቆይታ ያደረገው ተከላካይ ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

በ2018 የውድድር ዓመት ሽረ ምድረ ገነትን በመልቀቅ ወደ ወልዋሎ አምርቶ በግሉ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው የመሀል ተከላካዩ ነፃነት ገብረመድህን በቢጫዎቹ ቤት ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል። በተጠናቀቀው ዓመት ከቡድኑ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫ ያሸነፈው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በአሳዳጊ ክለቡ ሽረ ምድረ ገነት ፣ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በወልዋሎ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል።