ሴናፍ ዋቁማ ለታንዛንያው ክለብ ፈርማለች

ሴናፍ ዋቁማ ለታንዛንያው ክለብ ፈርማለች

ሲምባ ኩዊንስ ኢትዮጵያዊቷን አጥቂ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል

ባለፈው የውድድር ዘመን ወደ ሲምባ ኩዊንስ ለማቅናት ጥረት አድርጋ በጥቂት ቀናት መዘግየት ብቻ ክለቡ ማስፈረም ባለመቻሉ ዝውውሩ ሳይሳካላት የቀረችው ሴናፍ ዋቁማ አሁን በድጋሚ ከክለቡ ጋር ባደረገችው ንግግር መፈረሟን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ከዚህ ቀደም በጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ፣ አዳማ ከተማ ፣ መቻል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተለያዩ የዕድሜ እርከኖች የተጫወተችው እና በግሏ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆና ያጠናቀቀች እና የሊጉን ዋንጫ ያነሳችው አጥቂዋ በቀጣይ በታንዛኒያው ክለብ ሲምባ ኪዊንስ የምንመለከታት ይሆናል።