በረከት ሳሙኤል ወደ ቢጫዎቹ አምርቷል።

በትናንትናው ዕለት የነፃነት ገብረመድኅንን ውል ለማራዘም ተስማምተው ዛሬ ረፋድ ኢዮብ ዓለማየሁን የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚ ማድረግ የቻሉት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ የመሃል ተከላካዩ በረከት ሳሙኤልን የግላቸው አድርገዋል። ላለፉት አራት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ ማድረግ የቻለው ግዙፉ ተከላካይ ከዚህ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ መጫወቱ ይታወሳል።

