ቻምፒዮኖቹ የታዳጊ ቡድን ፍሬዎቻቸውን ውል አራዝመዋል

ቻምፒዮኖቹ የታዳጊ ቡድን ፍሬዎቻቸውን ውል አራዝመዋል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና  ወደ ዋናው ቡድን አድገው ጥሩ ጊዜ ያሳለፉት ወጣቶች ውላቸው ተራዝሞላቸዋል።

ለቀጣይ የውድድር ዘመን እና ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር አዳዲስ ተጫዋቾችን በማምጣት እና የነባር ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ላይ የሚገኙት የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡናዎች የሁለቱን የታዳጊ ቡድን  ፍሬዎቻቸውን አስቻለው ሙሴ እና መላኩ አሰፋ ውል አራዝመዋል።

ሁለቱም ወጣት ተጫዋቾች ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዋናው ቡደን በነበራቸው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በቋሚ አስራ አንድ አሰላለፍ እየገቡ እየተጫወቱ ሲገኝ ወደ ፊት የሚኖራቸውን ዕድገት ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በቡድኑ እንዲቆዩ ውላቸው እንደተራዘመ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።