በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉት ፈረሰኞቹ የመስመር አጥቂያቸውን ውል አራዝመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ተስፋ ሰጪ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው የመስመር አጥቂው ፀጋ ከድር በፈረሰኞቹ ቤት ለመቆየት መስማመቱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ሊጉ ሀላባ ከተማ ከተጫወተ በኋላ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሎ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በክለቡ ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ከክለቡ ለመቆየት ቆይታ ለማራዘም ተስማምቷል።

