በከፍተኛ ሊግ መድመቅ የቻለው የመስመር አጥቂው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመጫወት ተስማምቷል።

በወሎ ከቆንጆዎች ምድር ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ከተማ የተገኘው እና እግርኳሰን በክለብ ደረጃ በከፋ ቡና ፣ ሀላባ ከተማ እንዲሁም ዘንድሮ በደሴ ከተማ ስድስት ጎሎችን በማስቆጠር ስኬታማ ዓመትን ያሳለፈው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ቢላል ገመዳ መዳረሻው ፈረሰኞቹ ቤት ሆኗል። ቢላል ለሦስት ዓመት በፈረሰኞቹ ቤት የሚቆይ ይሆናል።
አስቀድመው የብሩክ እንዳለ እና ተመስገን ብርሃኑን ዝውውር ያጠናቀቁት ፈረሰኞቹ በቀጣይ ጊዜያት ሌሎች ዝውውሮች እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል።

