ሰጎኖቹ የሁለቱን ተጫዋቾች ዝውውር ይፋ አድርገዋል

ሰጎኖቹ የሁለቱን ተጫዋቾች ዝውውር ይፋ አድርገዋል

አስቀድመን በነገርናችሁ መረጃ መሰረት ነገሌ አርሲዎች ሁለቱን ተጫዋቾች የግላቸው ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።

የአሰልጣኝ ቱሉ ደስታን ውል በማራዘም እና የወሳኝ ተጫዋቾቹን ሮኆቦት ሰላሎ፣ ዳዊት ተፈራ እና አለኝታ ማርቆስን ውል ያራዘሙት ነገሌዎች የመጀመርያ ፈራሚዎቻቸውን መሐመድኑር ናስር እና ያሬድ ብሩክን እንዳደረጉ ገልፀን ነበር። በዚህም መሠረት ክለቡ አሁን የሁለቱን ተጫዋቾች ዝውውር ይፋ አድርጓል።

ነገሌ አርሲ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ስብስቡን አጠናክሮ ለመቅረብ በሚያደርገው ጥረት የቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል ማራዘሙ እንዳለ ሆኖ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስብ መቀላቀሉ የበለጠ ጠንካራ ቡድን እንደሚያደርገው ይገመታል።