የጦና ንቦቹ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈርመዋል

የጦና ንቦቹ ሁለገቡን ተጫዋች አስፈርመዋል

ከሁለት ክለቦች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው  ሁለገቡ ተጫዋች ወላይታ ድቻን ተቀላቅሏል።

በአምቦ ፕሮጀክት የጀመረው የእግርኳስ ሕይወቱን በኋላም በአዳማ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከመቐሌ ሰባ እንደርታ ቆይታ የነበረው ሱሌይማን ሐሚድ አሁን መዳረሻው ወላይታ ድቻ ሆኗል።

ለሁለት ዓመት ፊርማውን ያኖረው ሱሌይማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን ተጫዋቹ ለአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ቡድን ጥንካሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።