የ2017 የፕሪምየር ሊጉ ተስፋኛ ኮከብ ተጫዋች በቡናማዎቹ ቤት ውሉን አራዝሟል

የእግርኳስ ህይወቱ በኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ቡናማዎችን በወጥ አቋም ማገልገል የቻለው ወጣቱ ተስፈኛ ይታገሱ ታሪኩ በአሳዳጊው ቤት ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት መስማቱን አውቀናል። ተሰፈኛው አማካይ ይታገሱ በ2017 የሊጉ ተስፋኛ ኮከብ መባሉ ይታወሳል።
በአሰልጣኝ ገብረመድን ሀይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች አስቀድመው አቡበከር ኑራ፣ በረከት ወልደ ዩሐንስ እና አብዱልሰመድ የሱፍን የግላቸው ማድረጋቸው ሲታወቅ አሁን ደግሞ የይታገሱ ታሪኩን ውል ለማራዘም መስማማታቸውን አውቀናል። በተጨማሪም ቡናማዎች በቀጣይም ተጨማሪ ዝውውሮችን እንደሚፈፅሙ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ኢትዮጵያ ቡና ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ስብስቡን አጠናክሮ ለመቅረብ በሚያደርገው ጥረት የቁልፍ ተጫዋቹን ውል ማራዘሙ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ ነው።

