ምዓም አናብስት በፊፋ ውሳኔ ዙርያ መግለጫ አውጥተዋል

ከቀናት በፊት በ2017 የውድድር ዓመት ክለቡን ላገለገለው ካሜሮናዊ አጥቂ ማን ይክረ ዳንግሞ በ45 ቀናት ውስጥ ክፍያ እንዲፈፅሙ የተበየነላቸው መቐለ 70 እንደርታዎች በክስ ሂደቱ ዙርያ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፃቸው መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸውም መቐለ 70 እንደርታ ታግዷል በሚል የተሰራጨው ዜና የጉዳዩን ሙሉ ሂደት የማያሳይ መሆኑን በመግለፅ ውሳኔውም እንደታገደ ጠቅሰዋል።
ዛሬ ባወጣው መግለጫ “ከFIFA በ20 ጁላይ 2026 በተላከው ደብዳቤ መሠረት ክለባችን የDispute Resolution Chamber ውሳኔ ሙሉ ምክንያት እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥያቄ FIFA ተቀብሎታል። የውሳኔው ሙሉ ምክንያት እስኪላክ ድረስም በRSTP አንቀጽ 24 (5) (a) መሠረት የ45 ቀናት የክፍያ ጊዜ መቆሙን FIFA በግልጽ አሳውቋል” ያለው ክለቡ ጉዳዩ ገና በሕጋዊ ሂደት ላይ ነው ፤ የFIFA ደብዳቤም የሂደቱን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ እንጂ አዲስ የእገዳ ውሳኔ የሚያሳውቅ አይደለም” ብሏል።

