ኤሌክትሪክ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዝሟል

ኤሌክትሪክ የወሳኝ ተጫዋቹን ውል አራዝሟል

የ2018 የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በክለቧ ለመቆየት ተስማምታለች።

በውድድር ዓመቱ እጅግ ማራኪ እንቅስቃሴ በማድረግ ጭምር 24 ግቦችን አስቆጥራ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነችው ዳግማዊት ሰለሞን ከቡድኗ ጋር ለመቆየት መስማማቷን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች የነበረችው ዳግማዊት ለአንድ ዓመት የቆየችበትን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ለመመለስ የነበራት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደነበር ይታወቃል።