ነብሮቹ ሁለተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

ነብሮቹ ሁለተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል

በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው የግራ መስመር አጥቂው ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አቅንቷል።

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚመሩት ሀዲያዎች ቢኒያም ጌታቸውን የመጀመርያ ፈራሚያቸው በማድረግ ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን አሁን ኢዮብ ገብረማርያምን ሁለተኛ ፈራሚያቸው አድርገዋል።

ኢዮብ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ በኢትዮጵያ መድን ፣ በሻሸመኔ ከተማ እንዲሁም ያሳለፍናቸውን ሁለት ዓመታት ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ በማድረግ አሁን ለሁለት ዓመታት በነብሮቹ ቤት ለመጫወት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።