አዲስ አዳጊው ወደ ዝውውሩ ገብቷል

አዲስ አዳጊው ወደ ዝውውሩ ገብቷል


ሀላባ ከተማ የሁለት ጋናውያን ተጫዋቾችን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ የቻለው ሀላባ ከተማ ለመጪው የውድድር ዘመን ስብስቡን ለማጠናከር ሁለት ጋናውያን ተጫዋቾችን ለማስፈረም መስማማቱ ሶከር ኢትዮጵያ ማወቅ ችላለች። የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ፣ በኢትዮጵያ ቡና እና ባለፈው የውድድር ዘመን በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫውቶ ያሳለፈው እንዲሁም በቡና ቤት በነበረው ቆይታ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው አጥቂው ኮንኮኒ ሀፊዝ ነው።

ሌላኛው ሀላባ ከተማን ለመቀላቀል የተስማማው ጋናዊ ተጫዋች ደግሞ የመሃል ተከላካዩ ካሌብ አማንክዋህ ነው። ለሁገሩ ክለብ አክራ ሀርትስ ኦፍ ኦክ ፣ አዱአና ስታርስ እና ዌስት አፍሪካን ፉትቦል አካዳሚ ካሳለፈ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲጫወት የነበረው የመሀል ተከላካዩ አሁን ከአዲሱ አዳጊ ክለብ ጋር ለመጫወት የሚያስችለውን የፊርማ ስምምነት አጠናቋል። የሁለቱ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች መቀላቀል ለሀላባ ከተማ የፊት እና የኋላ ክፍል ተጨማሪ ጥንካሬን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።