ያለፈው አንድ ዓመት በሀድያ ሆሳዕና በምክትል አሰልጣኝነት ጋር የሰራው ደጉ ደበበ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ከፍ ያለ ስም ካላቸው የቀድሞ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ደጉ ደበበ በሀድያ ሆሳዕና በረዳት አሰልጣኝነት የስልጠና ህይወቱን መጀመሩ ይታወቃል።
ባለፈው አንድ ዓመት የአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ ረዳት የነበረው ደጉ አሁን ደግሞ ወደ አዳማ ከተማ አምርቶ ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ያሰለጠነውን የአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ምክትል አሰልጣኝ ለመሆን ወደ ክለቡ አምርቷል። አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በተጫዋችነት ፣ በክለብ እና በብሔራዊ ቡድን ያካበተውን ከፍተኛ ልምድ በማመን አብሮት እንዲሰራ እንደወሰነም አውቀናል።
ደጉ ደበበ ከአርባምንጭ ከተማ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ በርከት ያሉ በዋንጫ ያሸበረቁ ዓመታት ማሳለፉ ሲታወስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል በመሆንም ማገልገሉ ይታወሳል። በመጨረሻ ክለቡ ወላይታ ድቻ ተጫውቶ ጫማ ከሰቀለ በኋላም በአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕና በተለያዩ ሚናዎች ማገልገሉ ይታወሳል።

