ከኢትዮጵያ መድን ጋር ቆይታ የነበረው ብሩክ ሙልጌታ ወደ ባህር ዳር አምርቷል

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚሰለጥኑት ባህር ዳር ከተማዎች ከዚህ ቀደም ሽመልስ በቀለ፣ አስራት ቱንጆ፣ ዮዳሄ ዳዊት እና ኪቲካ ጅማን ማስፈረማቸው ይታወቃል አሁን ደግሞ የፈት መስመር ተጫዋቹ ብሩክ ሙሉጌታን ማስፈረማቸው ታውቋል። በኮልፌ ቀራንዮ፣ በኢትዮጵያ መድን ፣ በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂው ብሩክ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ዳግም ለኢትዮጵያ መድን ለአንድ አመት ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን ማረፊያው ባህር ዳር ከተማ ሆኗል።

