ግብ ጠባቂው ኢድሪሱ አብዱላሂ ከሰጎኖቹ ጋር ይቆያል

ግብ ጠባቂው ኢድሪሱ አብዱላሂ ከሰጎኖቹ ጋር ይቆያል

ባለፉት ሁለት ዓመታት ድንቅ ብቃት ካሳዩ ግብ ጠባቂዎች አንዱ የሆነው ጋናዊ ከነጌሌ አርሲዎች ጋር ይቀጥላል

በታንዛንያው አዛም የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ሀገራችን በመምጣት ለኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም በተጠናቀቀው ዓመት በነጌሌ አርሲ ቆይታ ያደረገው ጋናዊው ግብ ጠባቂ አብዱላሂ ኢድሪሱ ከሰጎኖቹ ጋር ካሳለፈው ስኬታማ ቆይታ በኋላ ውሉ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል። የውል ጊዜው መጠናቀቁን ተከትሎ ከበርካታ የሊጉ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ተጫዋቹ ማረፊያ ሰጎኖቹ ጋር እንዲሆን ምርጫው በማድረጉ ለሁለት ዓመት ለነጌሲ አርሲ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።