የመሀል ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳ ወደ ፋሲል ከነማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል
የዋና አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደ ጊዮርጊስ ውል ካራዝሙ በኋላ ጄሮም ፍሊፕን የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ለማድረግ ከስምምነት የደረሱት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ የዝውውር መስኮቱ ሁለተኛ ፈራሚ ለማግኘት ከስምምነት ደርሰዋል። ወደ ክለቡ ለማቅናት ከስምምነት የደረሰው ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ በግሉ ጥሩ ቆይታ የነበረው ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳ ነው።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ እና ዋናው ቡድን፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ሃዲያ ሆሳዕና፣ ባህርዳር ከተማ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም በኢትዮጵያ ዋና ብሔራዊ ቡድን እና ከኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ተከላካዩ አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የምዓም አናብስት ቆይታ በኋላ ወደ ዐፄዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

