ብርሃኑ አዳሙ ወደ ነብሮቹ አምርቷል

ብርሃኑ አዳሙ ወደ ነብሮቹ አምርቷል

ከመቐለ ሰባ እንድርታ ጋር ቆይታ የነበረው አጥቂ ማረፊያው ሀዲያ ሆሳዕና ሆኗል።

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ሚመሩት ሀዲያዎች ወደ ዝውውሩ በመግባት ቢኒያም ጌታቸው፣ ወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ያሬድ ታደሰ እና ኢዮብ ገብረማርያምን በማስፈረም የጄይላን ከማልን ውል በማራዘም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። አሁን ደግሞ ብርሃኑ አዳሙን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

በአርባምንጭ ከተማ እና ከከፍተኛ ሊግ በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው አጥቂው በምድረገነት ሽረ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ ሰባ እንደርታ በግሉ ጥሩ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። አጥቂው በነብሮቹ ቤት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።