ጋናዊው ወደ ሰጎኖቹ አመራ

ጋናዊው ወደ ሰጎኖቹ አመራ

አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል።

የአሰልጣኝ ቱሉ ደስታ እንዲሁም የወሳኝ ተጫዋቾቹ ርኆቦት ስላሎ፣ ዳዊት ተፈራ ፣ አለኝታ ማርቆስ እና እድሪሱ አብዱላሂ ውል አራዝመው መሐመድኑር ናስር ፣ ያሬድ ብሩክ ፣ ጀሚል ያዕቆብ እና እንዳልካቸው ጥበቡን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሰጎኖቹ አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው ዓመት በመቻል ቆይታ የነበረው ጋናዊ ኮሊንስ ኮፊ ኩድጆ የግላቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።

በሀገሩ ጋና ሱሱቢሪቢ ፣ ኮቶኮ ሮያልስ እና ንሶአትረማን ከተጫወተ በኋላ ወደ ሀገራችን በመምጣት በመቻል ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው ዓመት አራት ግቦች ማስቆጠሩ ሲታወስ አሁን ደግሞ ወደ ነጌሌ አርሲ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።