ጳውሎስ ከንቲባ ወደ ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል

ጳውሎስ ከንቲባ ወደ ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል

በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ የሚመሩት ቡናማዎቹ የግራ መስመር ተከላካዩን አስፈርመዋል።

በቀጣይ ዓመት ጠንካራ ቡድን ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ፣ በረከት ወልደዮሐንስ ፣ አብዱልሰላም የሱፍ ፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ድል አዲስ ገብሬን ለማስፈረም ተስማምተው የነባሮቹ አማኑኤል አድማሱ ፣ ይታገሱ ታሪኩ ፣ ኤርምያስ ሹምበዛ እና ረጂብ ሚፍታሕን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም መስማማታቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የግራ መስመር ተከላካዩን ጳውሎስ ከንቲባን ለመስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።

ከአርባምንጭ ምድር የተገኘው ጳውሎስ በንግድ ባንክ እና በመቻል ተስፋ ቡድን የተጫወተ ሲሆን በመቀጠል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያለፉትን ሁለት ዓመት ደግሞ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ አድርጎ መዳረሻውን ቡናማዎቹ ለማድረግ የተስማማ ሲሆን ነገ የህክምና ምርመራውን የሚያደርግ ይሆናል።