ቻምፕዮኖቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ቻምፕዮኖቹ ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ኢትዮጵያን ወክለው በሴካፋ የሴቶች ቻምፕዮንስ ሊግ የሚሳተፉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ሦስት ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የግብ ጠባቂያቸውን ውል አድሰዋል

በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው የ9 ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፕዮኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት እንዲሁም በቅርቡ ለሚያደርገው የሴካፋ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ይረዳው ዘንድ በርካታ ዝውውሮችን እያደረገ ይገኛል።

ቡድኑ በዛሬው ዕለትም የኢትዮ ኤሌክትሪኮቹን ማኅሌት ምትኩ እና በሻዱ ረጋሳ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማዋን ዓለምነሽ ገረመው በሁለት ዓመት ውል ሲያስፈርም የግብ ጠባቂዋን አበባ አጄቦ ውል ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት አራዝሟል።