ላለፉት 11 ዓመታት በነብሮቹ ቤት ቆይታ ያደረገው ሄኖክ አርፊጮ ውሉን አራዘመ

በአሰልጣኝ ሳምሶም አየለ እየተመሩ በቀጣይ የውድድር ዓመት እራሳቸውን ለማጠናከር ከዝውውር መስኮቱ ቢንያም ጌታቸው፣ ወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ያሬድ ታደሰ እና ብርሀኑ አዳሙ አስፈርመው የነባር ተጫዋቾችን ውል ያደሱት ነብሮቹ አሁን ደግሞ ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት በክለቡ የቆየውን የአምበሉ ሄኖክ አርፊጮ ውል አራዝመዋል። በዚህ ወቅት በፕሪምየር ሊጉ በአንድ ክለብ መለያ ለረዥም ዓመታት በማገልገል ቀዳሚ የሆነው የመስመር ተከላካዩ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በሀድያ ሆሳዕና የሚቆይ ይሆናል።

