ሀዋሳ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ።

የነባር ተጫዋቾችን ውል እያራዘመ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው የአሰልጣኝ ተመስገን ዳናው ሀዋሳ ከተማ የሁለት ነባር ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል።
ውሉን ያራዘመው አማካዩ ዳዊት ታደሰ ሲሆን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ከሐይቆቹ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል።
በዛሬው ዕለት ውሉን ያራዘመው ሌላኛው ተጫዋች ከታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ ወደ ሌላ ቡድን ሳያመራ ክለቡን ሲያገለግል የቆየው ቸርነት አውሽ ሲሆን ለአንድ ዓመት ከክለቡ ጋር እንደሚቆይ አረጋግጠናል።

