ፍሬው ሰለሞን አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

ፍሬው ሰለሞን አዲስ ክለብ ተቀላቀለ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ያሳለፈው አማካይ ወደ በርበሬዎቹ አምርቷል።

በአዲሱ የውድድር ዓመት ቡድናቸውን በማጠናከር የተጠመዱት አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች በዝውውር መስኮቱ ያላቸው የነቃ ተሳትፎ በማስቀጠል አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ያሳለፈው ፍሬው ሰለሞንን አስፈርመዋል።

በአምበልነት ባገለገለበት ክለብ በሰላሣ አምስት ጨዋታዎች አገልግሎ የኢትዮጵያ ዋንጫም ያሸነፈው ፍሬው ከዚህ ቀደም በሀላባ ከተማ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ መቻል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ወልዋሎ መጫወቱ ይታወሳል።