ሀላባ ከተማ የሌላኛውን ወሳኝ ተጫዋቸቻውን ውል አራዝመዋል።

አዲስ አዳጊዎቹ ሀላባ ከተማዎች የቡድናቸውን ወሳኝ ተጫዋቾች ውል ማደሳቸውን ቀጥለው አሁን አማካዩ ፋሲል አበባየሁ ለተጨማሪ ዓመት በቡድኑ የሚቆይበትን ውል አራዝመዋል።
በዲላ ከተማ የተገኘው እና በተለያዩ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች የተጫወተው አበባየሁ በሊጉ በደደቢት እና በወልቂጤ ከተማ የተመለከትነው ሲሆን ዘንድሮ ሀላባ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲገባ ጥሩ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን አሁን ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ስምምነት ፈፅሟል።

