ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ወደ መቻል አምርቷል

ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ወደ መቻል አምርቷል

በቅርብ ዓመታት ተስፋ ሰጪ ብቃት ያሳየው የመስመር ተከላካይ መቻልን ተቀላቅሏል

በሀዋሳ ከተማ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ17 እና 20 ዓመት በታች ቡድን እየተጫወተ ያደገው እና ከሁለት ዓመት በፊት ሀዋሳ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የክረምታዊ ውድድር የእግር ኳስ ውድድር ላይ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ መልማይነት ኢትዮጵያ መድን ተቀላቅሎ ከክለቡ ጋር ቻምፕዮን መሆን የቻለው የቀኝ መስመር ተከላካዩ በረከት ካሌብ ወደ መቻል አምርቷል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መቻልን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ቡድኑን ለማጠናከር ጠንካራ ዝውውሮች የፈፀሙ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የተወሰኑ ተጫዋቾች ቡድኑን ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።