ያለፉትን ሁለት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ቆይታ የነበረው የመስመር ተከላካይ ወደ ሀድያ አቅንቷል

በአሰልጣኝ ሳምሶም አየለ የሚመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ወደ ዝውውሩ በስፋት በመግባት የነባር ተጫዋቾች ውል በመራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ቡድናቸውን እያጠናከሩ ይገኛል። አሁን የቀኝ መስመር ተከላካዮን ቶሎሳ ንጉሴን ለሁለት ዓመት አስፈርመዋል። ከዚህ ቀደም በቡራዩ እንዲሁም በሀምበሪቾን ወደ በከፍተኛ ሊግ እና በፕሪምየር ሊም መጫወት የቻለው ቶሎሳ በመስመር ተከላካይነት እና በመስመር ተጫዋችነት መጫወት የሚችል ሁለገብ ተጫዋች መሆኑ ይታወሳል።

