ያለፉትን ስድስት ወራት ከባህር ዳር ጋር ቆይታ የነበረው አጥቂው ከቀረው አንድ ዓመት በተጨማሪ ሌላ አንድ ዓመት ለመቆየት አዲስ ውል አስሯል።

በአንደኛ ሊግ ለሻኪሶ ከተማ ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ወደ ኢትዮጵያ ቡና ካመጡት በኋላ ራሱን በሊጉ ማስተዋወቅ የቻለው ፈጣኑ አጥቂ አንተነህ በያዝነው ዓመት ስድስት ወሩን በሸገር ከተማ ቆይታ ካደረገ በኋላም ስድስት ወር ደግሞ ለባህር ዳር ከተማ ሲጫወት መቆየቱ ይታወሳል።
ከሸገር ወደ ባህር ዳር ሲመጣ ለጣና ሞገዶቹ ለአንድ ዓመት ለስድስት ወር ፈርሞ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን ምንም እንኳን አንተነህ ለባህር ዳር ለመጫወት ቀሪ አንድ ዓመት ቢኖረውም ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማለትም እስከ 2020 ሰኔ 30 ለመቆየት አዲስ የውል ማድረጉን አውቀናል።

