የ70ኛ ዓመት የምስረታቸው በማክበር ላይ የሚገኙት የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊዎቹ ወልዋሎዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በክለቡ ለማቆየት ከተስማሙ በኋላ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም በዝውውሩ ንቁ ተሳታፊ የነበሩት ወልዋሎዎች ከቀናት በኋላ ማክሰኞ ነሐሴ 12 የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል።
በትናንትናው ዕለት የካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ምዝገባቸው ያጠናቀቁት ቢጫዎቹ በውድድሩ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ከሱዳኑ አል ሂላል አል ሳሕል ጋር መደልደላቸው የሚታወስ ነው።

