በካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የሚጠብቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካዩን በጉዳት አጥቷል።

በሩዋንዳ ለሚካሄደው የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን ወደ ሩዋንዳ ለማቅናት በዝግጅት ላይ ሲሆን አማካዩዋን እመቤት አዲሱን በጉዳት ምክንያት ማጣቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
በትውልድ ቦታዋ አርባምንጭ ከተማ የእግርኳስ ጅማሮዋን ያደረገችው እመቤት በመቀጠልም በመቻል ከነበራት ቆይታ በኋላ ላለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መለያ እየተጫወተች ስትገኝ አሁን ደግሞ በገጠማት ጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ውጭ መሆኗን ታውቋል።

