ኤርምያስ ትግሬ ወደ ጋሞ ጨንቻ አምርቷል

ኤርምያስ ትግሬ ወደ ጋሞ ጨንቻ አምርቷል

ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ተጫዋች አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል

በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በሚሳተፉበት ፕሪምየር ሊግ ስብስባቸውን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉት እና በዝውውር መስኮቱ በአመዛኙ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ጥሩ ጊዜ ያሳለፉ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ የሚገኙት በአሰልጣኝ ማትዮስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች አሁን ደግሞ በመንጌ ቤንሻንጉል ቆይታ የነበረው ሁለገቡ ተጫዋች ኤርሚያስ ትግሬ አስፈርመዋል።

ከካማሼ ከተማ እግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ኤርሚያስ በመሐል ተከላካይነት እና አማካይ ተከላካይ ሆኖ መጫወት የሚችል ሲሆን ከዚህ ቀደም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ቆይታ አድርጎ አሁን ማረፊያውን አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ አድርጓል።