ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ተጫዋች አዲስ አዳጊዎችን ተቀላቅሏል።

በአሳዳጊ አሰልጣኛቸው ማትዮስ ለማ የሚመሩት ጋሞ ጨንቻዎች ብዙም ዕይታ ውስጥ ያልገቡ በተለይ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ጥሩ ጊዜ ያሳለፉ ተጫዋቾችን በማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለገቡን ተጫዋች ኤርሚያስ ትግሬ ከመንጌ ቤላሻንጉል አስፈርመዋል።
ኤርሚያስ ከካማሼ ከተማ እግር ኳስ ህይወቱን መነሻ ያደረገ ሲሆን በመሐል ተከላካይም ሆነ የአማካይ ተከላካይ በመሆን የሚጫወት ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ከመንጌ ቤላሻንጉል ጋር ቆይታ አድርጎ አሁን ማረፊያውን አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻ አድርጓል።

