ናይጄርያዊው ወደ ነብሮቹ አመራ

ናይጄርያዊው ወደ ነብሮቹ አመራ

ሀዲያ ሆሳዕናዎች ናይጄርያዊውን የመሃል ተከላካይ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሱ

በዝውውር መስኮቱ የበርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ቡድናቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ሀድያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ ናይ ናይጄርያዊው አፎላያን ፒተርስ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በቅርብ ተቃናቃኞቹ ኢንየምባ እና ሀርት ላንድ መጫወት የቻለው ይህ የ26 ዓመት ተከላካይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢንየምባ ጥሩ ቆይታ ማድረግ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ2023/24 ጀምሮ የተጫወተበትን የናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ በመልቀቅ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊጉ ሀድያ ሆሳዕናን ለማገልገል በአንድ ዓመት ውል ቡድኑን ተቀላቅሏል።