በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ከነጌሌዎች ጋር ቆይታ የነበረው ካሜሮናዊ ተከላካይ ውሉን ማራዘሙ ታውቋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ሀገራችን የመጣው እና ከሌላኛው የቡድኑ አጋር ቁመታሙ ተከላካይ ሮሆቦት ሶላሎ ጋር በመጣመር ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ግዙፉ ካሜሮናዊ ተከላካይ ዲሲሬ ፓስካል ለተጨማሪ ዓመት በሰጎኖቹ ቤት ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።
በሀገሩ ካሜሩን እግርኳስን የጀመረው ይህ ተከላካይ ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ክለቦች ስዊችባክስ እና ሳን አንቶንዮ እንዲሁም በቼክ ሪፐብሊክ ፣ በስዊድን እና በግሪክ ክለቦች ቪይስኮቭ ፣ አይኤፍኬ ሉላ እና ፔሪኮስ መጫወት የቻለ ሲሆን ቀጥሎም ወደ አህጉረ አፍሪካ በመምጣት በአል ሜሪል እና ቪታ መጫወት ችሏል። ሆኖም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ቆይታ ባደረገበት የሰጎኖቹ ቤት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውሉን አራዝሟል።

