ሀዲያ ሆሳዕናዎች ጋናዊውን አማካይ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሱ።

ቀደም ብለው ናይጄርያዊውን ተከላካይ አፎላያን ፒተርስ ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት እና በዝውውር መስኮቱ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ወደ 2019 የውድድር ዓመት ለመቅረብ በዝግጅት ላይ ያሉት ሀዲያ ሆሳዕናዎች አሁን ደግሞ ጋናዊው የተከላካይ አማካይ ፕሪንስ ባዱን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በኔሽንስ ባሳየው ጥሩ ብቃት ወደ አሻንቲ ኮቶኮ ተዘዋውሮ ከክለቡ ጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ በቅርቡ ከክለቡ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት ካፈረሰ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለሀዲያ ሆሳዕና ለመጫወት የአንድ ዓመት ውል ለመፈራረም ከስምምነት ደርሷል።

