መሐመድ ካማራ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደረሰው

መሐመድ ካማራ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደረሰው

አዲሱ የጦሩ የግብ ዘብ ለሀገራዊ ግዴታ ጥሪ ደርሶታል

በቅርቡ የመቻልን ግብ ለመጠበቅ ክለቡን የተቀላቀለው ጊንያዊ ግብ ጠባቂ መሐመድ ካማራ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ላሉበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለማገልገል ጥሪ ቀርቦለታል። በጊኒ እግር ኳስ ትልቅ ስም ያለውና ከ1998 እስከ 2013 ብሔራዊ ቡድኑን ያገለገለውን ወላጅ አባቱ ኪሞኮ ካማራን ፈለግ ተከትሎ ከ2021 ጀምሮ ብሔራዊ ቡድኑን በማገልገል ላይ የሚገኘው ግብ ጠባቂው በቀጣይ ሀገሩ ከደቡብ አፍሪካ እና ከኬንያ ጋር በምታደርጋቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለመካፈል ብሔራዊ ቡድኑን የሚቀላቀል ይሆናል።

የ26 ዓመቱ ካማራ በሀገሩ ክለቦች ካሉም እና ሶዋር ካገለገለ በኋላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በጋናው ኃያል ክለብ አሳንቴ ኮቶኮ ድንቅ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ለወጣት እና ለዋናው የጊኒ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል።