የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክስዮን ማሕበር የቦርድ አባላት እና የፕረዚዳት ምርጫ የሚካሄድበት ቀን ታወቀ

የምስረታ ሰባተኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የሀገሪቱን ቁጥር አንድ የሊግ ውድድር በበላይነት እየመራ እንደሚገኝ ይታወቃል። አክሲዮን ማኅበሩ የ2018 የውድድር ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ እሁድ መስከረም 10 በአዲስ አበባ ከተማ መደበኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ሰምተናል።
በጉባኤው ላይ የ2018 የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ2019 ዕቅድና በጀት እንዲሁም በ2019 ፕሪምየር ሊጉን ስለሚቀላቀሉ አዲስ አዳጊ ክለቦች አክስዮን አባልነት ሰነዶች አጀንዳ ሆነው ይቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዋናነት ግን ተሳታፊ ክለቦች እጨዎቻቸው ከላኩ በኋላ ለቀጣይ ዓመታት አክስዮን ማሕበሩን የሚመሩ የቦርድ አባላት እና የፕረዚዳት ምርጫ እንደሚካሄድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

