የሴራሊዮን ዜግነት ያለው ተጫዋች ሳይዱ ፎፋናህ ለጦና ንቦቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል::

ወላይታ ዲቻ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የአማካይ ክፍሉን ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴ የሴራሊዮን ዜግነት ያለውን ሳይዱ ፎፋናህን በይፋ የክለቡ አካል አድርጓል። በቅጽል ስሙ “ኦኮቻ” በመባል የሚታወቀው እና በመሃል ሜዳ እንዲሁም በተከላካይ አማካይ ቦታ ላይ የሚጫወተው ይህ ተጫዋች ለአዲሱ የውድድር ዘመን ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን የውል ስምምነት ፈጽሟል።
የእግር ኳስ ህይወቱን በሀገሩ ክለብ ካሎን ኤፍሲ የጀመረው ፎፋናህ በኋላም ወደ ሴኔጋሉ አስ ፒኪን፣ የካዛክስታኑ ዜቲሱ ታሊዲኮርጋን እና የካቲት 2026 ላይ ደግሞ የእስራኤሉን ሀፖኤል ራአናና በመቀላቀል ተጫውቷል። በተጨማሪም በ2021 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ላይ የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በወላይታ ዲቻ ማሊያ አዲስ የጨዋታ ምዕራፍ ለመጀመር ፊርማውን አኑሯል።

