ኢትዮጵያውያን ዳኞች የአፍሪካ U-23 ማጣሪያ ጨዋታን እንዲመሩ ተመርጠዋል

ኢትዮጵያውያን ዳኞች የአፍሪካ U-23 ማጣሪያ ጨዋታን እንዲመሩ ተመርጠዋል

የፊታችን ማክሰኞ በሞሪሸስ የሚደረገው የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን ዳኞች የሚመራ ይሆናል።

በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ይፋዊ መርሐግብር መሠረት መስከረም 26 / 2019 ዓ/ም በሞሪሸስ ኮት ዲኦር ናሽናል ስፖርትስ ኮምፕሌክስ በሚካሄደው የ2026 U-23 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሞሪሸስ እና ዚምባብዌ ጨዋታ ላይ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ተመድበዋል። በዚህም ኢንተርናሽናል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ ዋና ዳኛ ሆኖ ሲሰየም፣ ኢንተርናሽናል ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት እና ኢንተርናሽናል ዳኛ ዘመኑ ሲሳይነው ደግሞ በረዳት ዳኝነት ያገለግላሉ።

በተጨማሪም ኢንተርናሽናል ዳኛ ሃይማኖት አዳነ በአራተኛ ዳኝነት የተመደበ ሲሆን የጨዋታው ኮሚሽነር ከኮሞሮስ እንዲሁም የዳኞች ገምጋሚ ከደቡብ አፍሪካ ተሰይመዋል። ጨዋታው በኢትዮጵያ አቆጣጠር ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ይሆናል።