ከዋልያዎቹ ስብስብ አንድ ተጫዋች በሌላ ተተክቷል

ከዋልያዎቹ ስብስብ አንድ ተጫዋች በሌላ ተተክቷል

ከደቂቃዎች በፊት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች አንድ አጥቂ በጉዳት ምክንያት ከስብስብ ውጪ ሲሆን በምትኩ ለሌላ ተጫዋች ጥሪ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርጋቸው የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ የተደረገ ሲሆን አሁን ፌዴሬሽኑ ይፋ ባደረገው መረጃ ደግሞ የሲዳማ ቡናው አጥቂ አቤል ያለው ጉዳት በማስተናገዱ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ  አዲስ ጥሪ መሠረት በሸገር ከተማው አጥቂ ቢኒያም ፍቅሩ ተተክቷል።

ቢኒያም ፍቅሩ ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በፊት በሜዳዋ ከሴኔጋል ጋር ባደረችው ጨዋታ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ የቻለ ሲሆን የመጀመሪያ ጥሪ ላይ አለመካተቱ ብዙዎችን ለደቂቃዎች ሲያነጋግር የነበር ጉዳይ ነበር።