ሸገር ከተማ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊካዊ ተከላካይ አስፈርሟል

ሸገር ከተማ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊካዊ ተከላካይ አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ዶ/ር ኢያሱ መርሐጽድቅ የሚመሩት ሸገር ከተማዎች የመሐል ተከላካይ ማስፈረማቸው ታውቋል።

በአምስት ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በአምስት ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሸገር ከተማዎች የኋላ የሜዳ ክፍላቸውን  ለማጠናከር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜግነት ያለው ጆን ኒካዲዮ የተሰኘ የመሐል ተከላካይ ማስፈረማቸው አውቀናል።

ኔካዲዮ በእግር ኳስ ሕይወቱ የቤልጂየሙን ስታንዳርድ ሊግ እና አርኤፍሲ ሴሬንግ ክለቦችን በመወከል የአውሮፓ እግር ኳስ ልምድ ያካበተ ሲሆን፣ በታንዛኒያ የሲንጊዳ እና በኮንጎ የኤፍሲ ሴንት ኢሎይ ሉፖፖ ተጫውቷል። በተጨማሪ የዲ.ሪ. ኮንጎ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ መጫወት ችሏል።

የ24 ዓመቱ ተጫዋች ወደ 1.94 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ይህ ተከላካይ በአካላዊ ጥንካሬው ሆነ በአየር ላይ ባለው የኳስ ብቃት እና በመከላከያ አያያዙ ከዚህ ቀደም የሚታወቅ ነው።